ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ጋር ተወያዩ

AMN ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ጋር የአዲስ አበባን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሻሻል በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በከተማ አስተዳደራችን የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በተለይ E- mobility (የጭስ አልባ ትራንስፖርት) ተደራሽነትን ለማስፋፋት እየሰራን ያለነውን ስራ ለማጠናከር እና በዘርፉ የተሰማሩ የግል ሴክተሮችንም ለመደገፍ ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት እና በትብብር ለመስራት ከማርያም ሳሊም ጋር ተግባብተናል ብለዋል።

ማርያም ሳሊምን እና የቴክኒካል ቡድናቸውን በራሴና በከተማው ህዝብ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review