ሕገ ወጡ የህወሐት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ

You are currently viewing ሕገ ወጡ የህወሐት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ

AMN ሐምሌ 11/2018

ሕገ ወጡ የህወሐት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው ሲሉ የስምረት ፓርቲ ሊቀ መንበር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ህዘብ ላይ የሚፈፅመውን አፈናና ጭቆና የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ህገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርግ በተደራጀ መልኩ ልንታገለውና ድምፃችን ልናሰማ ይገባል።

ሕገ ወጡ የህወሐት ቡድን ወጣቶችን ወደ ሱዳን መሸጥ ያቁም ያሉ ሲሆን ቡድኑ የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አሁን ላይ የፕሪቶርያው ስምምነት ለትግራይ ህዝብ ያመጣው እፎይታ መገታቱን አስታውሰው የተገኘውን ለውጥ በመቀልበስ የጊዜያዊ አስተዳደሩን በመንፈቅለ መንግስት ማውረዱና ራሱ መሾሙን አንስተዋል።

ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በዚህ ሳያበቃ ወጣቶችን በግዳጅ ለውትድርና በመመልመል ሕዝብን ለዳግም እልቂት ለመዳረግ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።

ህገ-ወጡ የህወሓት ቡድን እናቶች ልጆቻቸው ከእቅፋቸው በመንጠቅ ወደ ጦር ካምፕ በማስገባትና እናቶች በማሰር ኢሰብአዊ ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review