ቀጣዩ የበጀት ዓመት ብልፅግናዊ አሻራችንን በሁሉም መስኮች የምናሳርፍበት ነዉ – አቶ አደም ፋራህ

AMN ሐምሌ 15/2018

ቀጣዩ የበጀት ዓመት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር የምናረጋግጥበትና ደማቅ ብልፅግናዊ አሻራችንን በሁሉም መስኮች የምናሳርፍበት ሊሆን ይገባል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረካችንን በስኬት አጠናቀናል ብለዋል።

በዚህ መድረክ የአፈጻጸም ውጤቶቻችንን በጥልቀት ገምግመናል፤ በቀጣይም የሕዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ሲሉ ገልጸዋል።

ለ3 ቀናት የተካሄደው መድረክ ዓላማውን ባሳካ፣ እጅግ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ የማዘጋጀት ሚናውን በሚገባ ለተወጣው የአዲስ አበባ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ቀጣዩ የበጀት ዓመት የጋራ መግባባት የፈጠርንበትን ዕቅድ መሠረት በማድረግ፣ ከምርጫ ማግስት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር የምናረጋግጥበትና ደማቅ ብልፅግናዊ አሻራችንን በሁሉም መስኮች የምናሳርፍበት እንዲሆን ለአመራራችንና ለአባላቶቻችን ከአደራ ጭምር ማሳሰብ እወዳለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review