ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከካሜሮን አቻቸው ጋር ተወያዩ

AMN ሐምሌ 23/ 2018 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ምቤላ ምቤላ በሁለትዮሽ እና አሕጉራዊ ጉዳይ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ ሁለትዮሽ ግንኙነትን በተመለከተ ኢትዮጵያ እና ካሜሮን ጠንካራ እና ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

60ኛ ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን ለማክበር ዋዜማ ላይ ባሉበት ወቅት ሁለቱ አገራት ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ባሻገር ጠንካራ የኢኮኖሚ ግንኙነት ማዳበር በሚችሉበት መስክ መክረዋል።

የካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ምቤላ ምቤላ ኢትዮጵያ 49ኛው የአፍሪካ ኀብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባን በስኬት ማጠናቀቋን እና በተለይ ኢትዮጵያ ኀብረቱን በፋይናንስ ለማጠናከር ያሳለፈችውን ውሳኔ እና አቋም በማድነቅ ድጋፋቸውን መግለጻቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review