በአማራ ክልል የግብርና ምርታማነት ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing በአማራ ክልል የግብርና ምርታማነት ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር)

AMN- ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በክልሉ ከለውጡ ወዲህ በተለይ በግብርናው ዘርፍ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

በዘርፉ በተሰራው ሰፊ ስራ ከለውጡ በፊት በዓመት 90 ሚሊየን ኩንታል ገደማ ይመረት የነበረው የክልሉ አጠቃላይ የሰብል ምርት፣ በአሁኑ ወቅት ከ205 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማሳደግ ተችሏል፡፡

ለዚህም የመስኖ አጠቃቀም፣ የማሽነሪና ማዳበሪያ አቅርቦት፣ እንዲሁም ከለውጡ በፊት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የግድብ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዘርፍ የክልሉ የኤሌክትሪክ ሽፋን ከነበረበት 25 በመቶ ወደ 40 በመቶ ማደጉን አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ዓመታት የነበሩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ፈተናዎችና እንቅፋቶች እያሉ የተከናወኑት ስራዎች ከዚህ ቀደም ከተሰሩት በብዙ እጥፍ የሚበልጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የህዝቡን የመልማትና የመጠቀም ጥያቄዎች በተሟላ መንገድ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review