በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል አገራዊ መርሃ ግብር በአዲስ አበባም በሰፊ ንቅናቄ እየተተከለ ነዉ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል አገራዊ መርሃ ግብር በአዲስ አበባም በሰፊ ንቅናቄ እየተተከለ ነዉ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ እንኳን ለ8ኛ ዙር የአረንጋዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ቀን አደረሰን ! በማለት ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል አገራዊ ንቅናቄ አዲስ አበባችንም በሰፊ ንቅናቄ የተተከለ ነዉ ብለዋል፡፡

ለአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብሩ 176 የሚሆኑ ቦታዎች ተለይተዋል። የሚተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን በሚጨምር መልኩ በባለሙያ እየተገዘ በመከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የምንተክላው ተስፋን ፤ የኢትዮጵያ ብልፅግና፥ ለነገ ትውልድ የምናስተላልፈው ለምለሟ ኢትዮጵያን በምናባችን አይተን፥ በሃሳብ አንድ ሆነን፥ በተግባራችን በእጆቻችን ተክለን ውዷ ሃገራችን አረንጓዴ እያለበስናት ነው።

የምንተክለው ምግባችን፥ ጥላ፥ ውበት ነው። እየተከልን ያለነው ነገ በአየር መዘባት ምክንያት የሚወጣውን የብክለት፥ የጤና ችግር፥ የጎርፍ አደጋን አስቀድመን ለመከላከል ነው።

የአረንጓዴ አሻራ ህጻናት፥ ወጣቶች፥ ሴቶች አዋቂዎች ፥ አዛውንቶች በጋራ የምናሳካው ነው ። የተከልነውን በጋራ እንክባከብ፥ እንጠብቅ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review