በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አዲስ አበባ ከተከላ ወደ እንክብካቤ ፊቷን አዙራለች- ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አዲስ አበባ ከተከላ ወደ እንክብካቤ ፊቷን አዙራለች- ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN- ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በፒኮክ ፓርክ አስጀምረዋል።

መዲናዋ ባለፉት 7 ዓመታት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከሏን የገለጹት ምክትል ከንቲባው፣ በጊዜ ሂደት ከተከላ ወደ እንክብካቤ ፊቷን ማዞሯን አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ከብዛት ወደ ጥራት እና ከአካባቢ ጥበቃ ወደ ኢኮኖሚ ጥቅም ማሻገር ላይም እየሰራች መሆኗን አስረድተዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እስከ አሁን በክረምቱ ወራት በርካታ ችግኞች መተከላቸውን የገለጹት የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር)፣ በእዚህም የእቅዱን 92 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን፣ ይህ አጠቃላይ እቅዱን ከሚጠበቀው በላይ ለማሳካት እንደሚያስችለውም ተናግረዋል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review