የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከጣሊያኑ ማርኬ ሪጅን እና ከኤ ፒ ኤ-ሲ ቪ ኤምጋር የ1 ቢሊየን ብር ስምምነት ተፈራረመ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከጣሊያኑ ማርኬ ሪጅን እና ከኤ ፒ ኤ-ሲ ቪ ኤምጋር የ1 ቢሊየን ብር ስምምነት ተፈራረመ

‎AMN- ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከጣሊያኑ የማርኬ ሪጅን (Marche Region) እና ለአፍሪካ የልማት አጋርነት ከሚሠራው ኤ ፒ ኤ-ሲ ቪ ኤም (APA-CVM) ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚቆየውና በጣሊያን ማርኬ ሪጅን መንግሥት በገንዘብ የሚደገፈው ይህ ፕሮጀክት 1 ቢሊየን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን በዋነኝነት በሦስት ዋና ዋና መስኮች ላይ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል።

የቲቬት ተቋማትን አቅም መገንባት፣ የሰልጣኞችንና የአሰልጣኞችን የሙያ ክህሎት ማሳደግ፣የቁሳቁስና ቴክኖሎጂ ድጋፍ፣ ለተቋማቱ አስፈላጊ የሆኑ የመማሪያና የሥልጠና ግብዓቶችን ማሟላት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶችና ባለሙያዎች የሥራ ዕድልና የገበያ ትስስር ማመቻቸት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራባቸው መስኮች ናቸው፡፡

የመግባቢያ ሥምምነቱን በቢሮው የውጤት ተኮር ሥልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ፣ የኤ ፒ ኤ ሲ ቪ ኤም የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ተወካይ ጆናታን አስካኒ እና የማርኬ ሪጅን የዓለም አቀፍ ትብብር አስተባባሪ ናታሊኖ ባርቢዚ ፈርመውታል፡፡

የሲ ቪ ኤም (CVM) በኢትዮጵያ ምክትል ተጠሪ አቶ ኃይሉ ታደሰ፤ድርጅታቸው በኢትዮጵያ በልማት ዘርፍ ላለፉት 47 ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየ የጣሊያን ግብረ-ሠናይ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል ከቢሮው ጋር የነበሩ የሁለት ዓመታት አጫጭር ፕሮጀክቶች በስኬት መጠናቀቃቸውንም እንደገለጹ የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተፈረመው ስምምነት በበጀት መጠኑ ሰፊ መሆኑን በመግለጽ የማርኬ ሪጅን በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው የምትታወቅ በመሆኗ ፕሮጀክቱ ትልቅ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ዕድል እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት ተተግብሮ የታለመውን ውጤት እንዲያመጣ ቢሮው በበላይነት አስፈላጊውን ክትትልና በየጊዜዉ ቁጥጥር እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡ ቢሮዉ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ጥሪ አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review