የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከቡና ባሻገር

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከቡና ባሻገር

AMN- ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም

ሲኤንኤን በኢትዮጵያ ዙሪያ በሳምንቱ መጨረሻ ሰፊ ዘገባ አስተላልፏል።

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ታሪክ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ አምና መሪነቱን ለወርቅ አስረክቧል።

የአሜሪካው ቴሌቪዥን ሲኤንኤን ኢትዮጵያን ከቡና ውጪ ሲል ኢኮኖሚዋን የተመለከተ ዘገባ “ኮኔክቲንግ አፍሪካ” በሚለው ዝግጅቱ ያሰራጨውም ይህንን መነሻ አድርጎ ነው።

ዘጋቢዋ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ለዘገባዋ ሶስት ስፍራዎችን የጎበኘች ሲሆን፣ በምዕራብ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና የኩርሙክ ወርቅ ማምረቻ ፕሮጀክትን ተመልክታለች፡፡

በመሀል ኢትዮጵያ ደግሞ አዲሱ የቢሾፍቱ ግዙፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክትን ጎብኝታለች።

የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ዳሰሳውም፣ ኃይል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘዋሪ፣ የኤክስፖርትና የቀጣናዊ ትስስር አቀጣጣይ መሆኑን አጉልቶ አሳይቷል፡፡

በቅርቡ ምርት የሚጀምረው የኩርሙክ ወርቅ ማምረቻ ፕሮጀክት ደግሞ ከ600 ሚሊየን ዶላር በላይ የፈሰሰበት ትልቁ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሆኑ ተጠቅሷል።

ወርቅ ዘንድሮ 5.5 ቢሊየን ዶላር በማስገኘት ቡናን በ2.4 ቢሊየን ዶላር የበለጠ ሲሆን፣ ግዙፉ የኩርሙክ ወርቅ ማምረቻ ፕሮጀክት ብቻውን በዓመት 9 ቶን ወርቅ የማምረት አቅም እንዳለው እና ለኢትዮጵያ ከ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያስገኝላት ይጠበቃል።

የግዙፉ ኩርሙክ ወርቅ እውን መሆን በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲሳቡ ምክንያት መሆኑንም ዘገባው አትቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review