ከ38 ዓመታት ጥበቃ በኋላ የተበሰረ የወርቅ ፋብሪካ፤

በዓመት 9 ቶን ወርቅ የሚያመርት፣ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስገኝ፤
ከ600 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት የተደረገበት፤
በጥናት ላይ የነበረውን የወርቅ ፍለጋ ሂደት በመረከብ፣ ጥልቅ ጥናት በማድረግና የወርቅ ማምረቻ ፕሮጀክቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ ኢትዮጵያ የዓለም የወርቅ ካርታ ላይ ስሟ አንዲሰፍር አድርጓል፤
በአሜሪካና ካናዳ ስቶክ ማርኬት የተመዘገበ አስተማማኝና ታላቅ ዓለም ዓቀፍ ኢንቨስትመንት ነው።
ኢትዮጵያውያን ባለድርሻዎችን ያቀፈ፣ በኢትዮጵያውያን ማኔጅመንትና ባለሙያዎች የጎላ ሚና የሚመራ፤
ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት በመሆን፣ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን ያሳየ፤
የአካባቢውን ማህበረሰብ ያቀፈ፣ ለወጣቶች እውቀትና ስራ የፈጠረ፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ፣ የኩርሙክ ወረዳ እና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፈርጥ ነው።
የአካባቢ ደህንነትን ያከበረ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ፣ እጅግ ዘመናዊ ፕሮጀክት ነው።