ከ43 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠቱን ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ አስታወቀ

AMN- ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም

በ2018 በጀት አመት ከ43 ሚሊየን በላይ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠቱን ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ድርጅት አስታውቋል፡፡

በ2017 በአዲስ አበባ ከተማ በ100 የኤሌክትሪክ አውቶብሶች አገልግሎት መሰጠት የጀመረው ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከ43 ሚሊየን በላይ ተሳፋሪዎችን ማጓጓዙን የግሪን አዲስ (ቬሎሲቲ) ትራንስፖርት ዋና ሥራ አስኪያጅ ግዛው ዓለሙ ለኤ ኤም ኤን ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ከስምሪት እስከ ክፍያ ሥርዓቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡ ይሄም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ተቋሙ የዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀሙ በበጀት አመቱ የተሻለ ሥራ ለመስራት እንዳስቻለው ዋና ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

በረውዳ ሸምሱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review