AMN – ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፤ ባለፉት ጊዜያት የከተማዋን ሰላም ለማጽናት በተሠሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶች አፍራሽ መልእክቶችንና ሐሰተኛ መረጃዎችን በመመከት፣ ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመጠቀም አብሮነትን እና አንድነትን ማጠናከር እንዳለባቸው አቶ ብርሃኑ አጽንኦት ሰጥተው አስገንዝበዋል።
በሰላም ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድወሰን መኮንን በበኩላቸው፣ ወጣቶች ለአካባቢያቸው እና ለከተማቸው ሰላም ዘብ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት፣ የከተማዋን ሰላምና ልማት ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
በቴዎድሮስ ይሳ