AMN- ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም
የምክክር ሂደቱ ለአብሮነት ትልቅ እድል ከመፍጠር ባሻገር የሃገርን ዘላቂ ሰላምና አንድነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
የምክክር ጉባዔው ተሳታፊዎች ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በተለያዩ እሳቤዎች ላይ እና በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ምክክሩ ትልቅ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
የምክክር ሂደቱ የሃሳብ ነፃነት የተሞላበት መሆኑን ጠቅሰው አንዱ የአንዱን ሃሳብ በማክበር ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን ሃሳብ እያዋጡ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህም ምክክሩ እርስ በርስ የተዋወቅንበት እና የአንዱ ችግር ሌላው ላይ እንዳለ ያየንበት፣ ሃሳብ የተለዋወጥንበት ነው ሲሉም የጉባዔው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

በምክክሩ ሂደት እየተሰጡ የሚገኙ ሃሳቦችም ለዘላቂ ሀገር ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የምክክር ጉባኤው ችግሮች ላይ አሳታፊ በሆነ መንገድ በመምከር ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገ የሚበጅ ዘላቂ መፍትሄ ለማስቀመጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን ስር የሰደዱ አለመግባባቶችንና ልዩነቶችን ለመፍታት፣ ጠንካራ የፖለቲካ ሥርዓት ለመፍጠር እና ኢትዮጵያን በትብብር ለመገንባት እየተመካከሩ ይገኛሉ፡፡
ከሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከሁሉም የሃገሪቱ ክፍል እና ከዳያስፖራው የማህበረሰብ የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአንድነት በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ ቆይተዋል።
በአሁኑ ሰዓትም ለኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሄ ያሏቸውን ሃሳቦች በማመላከት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።
የሻምበል ምህረት