ከተግዳሮቶች ወደ ብሩህ ተስፋ እና የጋራ ራዕይ

AMN- ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም

May be an image of one or more people and dais

ኢትዮጵያ በታሪኳ አዳዲስ ምዕራፎችን በመክፈት፣ የውይይትና የሰላም ባህልን በማጎልበት ረገድ ትልቅ እመርታ እያሳየች ትገኛለች።

ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን በጥይት ሳይሆን በውይይት እንዲሁም በመደማመጥ ባህል መፍታት እንደምትችል አረጋግጣለች።

በዚህም ኢትዮጵያ ከተግዳሮቶች ወደ ብሩህ የተስፋ መንገድ እያመራች ሲሆን ዜጎቿም ካለፈው ትምህርት ወስደው በላቀ ጥንካሬ የምክክር ስኬትን አብስረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ለትውልድ የሚተርፍ የተረጋጋች እና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት ቁልፍ መሠረት ጥለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የተደረጉ ሰፊ ሀገራዊ የውይይት መድረኮች ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ሐሳብን በሰላማዊ መንገድ በነፃነት ማራመድ እና የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መቻሉም የፖለቲካ ከባቢውን ያረጋጋዋል፡፡

ከማህበረሰቡ ዕውቀትና ተሞክሮ በመነሳት የተደረጉ ውይይቶች የፖሊሲ እና የልማት አቅጣጫዎች የሕዝቡን ፍላጎት በቀጥታ እንዲያንጸባርቁ አስችለዋል።

ምክክሮች ማስተዋል የሰፈነበት ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር በማድረግ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን ሰላም ሲረጋገጥም የልማት እንቅስቃሴዎች ፍጥነታቸው ይጨምራል።

ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች ያለምንም ስጋት በልማት ስራዎች ላይ እንዲያተኩሩ ዕድል ፈጥሯል።

የወጣቶች እና የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሰፋ መደረጉ ለነገን ትውልድ ተስፋ ሰጭ ነው፡፡ ውይይት የጠብ መፍቻ ብቻ ሳይሆን የነገን ትውልድ ዕጣ ፈንታ በጋራ የመቅረጫ መንገድ ነው።

ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ አልፋ ያገኘችው የመግባባት ልምድ ሀገሪቱ ወደፊት የምታስመዘግበውን ሁለንተናዊ ድል የሚያበስር እና የነገን ቀና መንገድ የሚጠርግ ብሩህ ተስፋ ነው።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review