መጪዎቹን በዓላት መሰረት በማድረግ ዩኒየኖች ምርቶችን ለመሰረታዊ ማህበራት እያሰራጩ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing መጪዎቹን በዓላት መሰረት በማድረግ ዩኒየኖች ምርቶችን ለመሰረታዊ ማህበራት እያሰራጩ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ዩኒየኖች ምርቶችን በመጋዘኞቻቸው በማከማቸት ለመሰረታዊ ማህበራት እያሰራጩ መሆኑን የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ የዩኒየን ስራ አስኪያጆች እና የቦርድ ሰብሳቢዎች ጋር በምርት አቅርቦትና ስርጭት ላይ አስቀድሞ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሽታዬ መሐመድ እንደተናገሩት፣ በበዓላት ወቅት አባላትም ሆኑ የከተማው ነዋሪ እንዳይቸገር አስፈላጊ የሚባሉ የፍጆታ ምርቶች በተለይም የግብርና እና ኢንዱስትሪ እንዲሁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ እጥረት እንዳይከከሰት ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ዩኒየኖች ምርቶችን በመጋዘኞቻቸው በማከማቸት ለመሰረታዊ ማህበራት እያሰራጩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ማህበራቱ በዋጋም ሆነ በአቅርቦት ከነጻው ገበያ በተሻለ አግባብ ማቅረባቸውን የተናገሩት ኮሚሽነሯ፣ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን ምርቶች በአቅራቢያው በሚገኙ የማህበራቱ ሱቆች መሸመት እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡

ማህበራቱ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በፈጠረላቸው ትስስር መሰረት ለበዓላቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን በተለይም ጤፍ፣ የጥራጥሬ አህሎች፣ ዘይት፣ ሽንኩርት፣ እንቁላልና ዱቄት የመሳሰሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀናል ማለታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review