የትግራይ ሕዝብ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ፈጣን ምርጫ ይካሄዳል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የትግራይ ሕዝብ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ፈጣን ምርጫ ይካሄዳል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ኅዳር 17/2019 ዓ.ም

በትግራይ ክልል ሕዝቡ ራሱን የሚያስተዳድርበትን ፈጣን ምርጫ ማካሄድ የመንግሥት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

በማብራሪያቸውም፣ ታታሪና ሰላም ወዳድ የሆነው የትግራይ ሕዝብ በውስጡ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር በትብብር የመልማት ፍላጎቱ ተጎድቶ መቆየቱን አንስተዋል።

ባለፉት ጊዜያት መቃረንን እንደ ጀግንነት በመቁጠር የትግራይን ወጣቶች ለአደጋ እየዳረጉ የራሳቸውን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም የሚጥሩ አካላት እንደነበሩ ጠቁመዋል።

በሰላም ጊዜ የሚፎክሩ ሰዎች አስገዳይ እንጂ ሟች አይደሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ግን ሕዝቡ እውነታውን ተረድቶ ወደ ሰላማዊ ጉዞው እየተመለሰ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም መንግሥት የአየር ትራንስፖርት፣ ስልክ፣ ባንክ፣ ነዳጅና የመንግሥት ቢሮዎችን ወደ መደበኛ ሥራ እንደሚመልስ ገልጸው፣ ሰብዓዊ ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በሚቀጥለው ምርጫ የትግራይ ሕዝብ የተሻለውን መርጦ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገባውን ውክልና እንዲያገኝና ክልሉ በተመረጡ አመራሮች እንዲተዳደር እንደሚደረግ አብራርተዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review