የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት ያደረገ የንግድ ትርዒትና ባዛር በአዲስ አበባ ተከፈተ

You are currently viewing የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት ያደረገ የንግድ ትርዒትና ባዛር በአዲስ አበባ ተከፈተ

AMN – ኅዳር 16/2019 ዓ.ም

21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የንግድ ትርዒትና ባዛር የአራዳ ክፍለ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በይፋ ተከፍቷል።

የንግድ ትርዒትና ባዛሩን በአራዳ ክፍለ ከተማ በይፋ የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እንዲሁም የከተማዋ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ናቸው።

በመክፈቻው ወቅት ንግግር ያደረጉት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ ለከተማዋ ነዋሪዎች ገበያን የማረጋጋት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ባዛሩ አምራቾችና ድርጅቶች ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለሸማቾች እንዲያቀርቡና እንዲያስተዋውቁ ዕድል እንደሚፈጥር የገለጹት ምክትል ከንቲባው፤ ይህም የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ለማሳደግና ሸማቹ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና በአማራጭ እንዲገዛ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመላክተዋል።

የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፣ የንግድ ትርዒትና ባዛሩ በከተማዋ ያሉ አምራቾች የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

በንግድ ትርዒቱና ባዛሩ ላይ ከአዲስ አበባ እና ከአጎራባች ከተሞች የተውጣጡ አምራቾችና ድርጅቶች የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና ልዩ ልዩ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በብዛትና በጥራት ለሸማቾች አቅርበዋል።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተከፈተው ይህ የንግድ ትርዒትና ባዛር ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review