አብሮነትና ትብብርን የሚያጎላው መውሊድ በዓል

AMN – ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም

የእስልምና እምነት ተከታዮች በየዓመቱ በድምቀት ከሚያከብሯቸው በዓላት መካከል የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት ቀን መውሊድ በዓል አንዱ ነው።

በየዓመቱ በረቢዑል አወል ወር የሚከበረው ይህ ዕለት፣ የነቢዩን መወለድ ብቻ ሳይሆን የህይወት ጉዟቸውን፣ ሰብአዊ እሴቶቻቸውን እንዲሁም የመተሳሰብና የሰላም አስተምሮዎቻቸው የሚታወሱበት ታላቅ ዕለት ነው።

በበዓሉ የነቢዩን ታሪክ የሚዘክሩ ኪታቦች መቅራት፣ ሶላት መስገድ እና መሰል ሃይማኖታዊ ተግባራት ይከናወናሉ።

መውሊድ ከኢትዮጵያውያን ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ጋር አብሮ የሰረጸ ታሪካዊ በዓል ነው።

የመውሊድ በዓል የሚከበረው ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ በርካታ ሰብዓዊ ተግባራት በማከናወን ነው።

በዚህ ዕለት ለአቅመ ደካሞች እና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ምግብና መሰል እርዳታ ማድረግ የበዓሉ አንዱ ውብ እሴት ነው።

በተጨማሪም የእስልምና እምነት ተካታዮች የሆኑ በዓሉን ሲያከብሩ ዘመድ አዝማድን በመጠየቅ፣ እንግዶችን በማስተናገድ እና ሰላም በመመኘት ቀኑን በደስታ ያሳልፉታል።

በመውሊድ የእምነቱ አባቶችና ምዕመኑ ስለ ሀገር ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት ጸሎት የሚያደረጉ ሲሆን፤ ሀዲሶች እየተነበቡ በመንዙማ በድምቀት ተከብሮ ይውላል።

ዛሬ የሚከበረው 1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) እንደ ወትሮው ሁሉ በመተሳሰብና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል፡፡

በበረከት ጌታቸው

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review