ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ

AMN – ኅዳር 17/ 2019 ዓ.ም

የ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ይካሄዳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው መነሻ የሚያደርጉት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 በጀት ዓመት የመንግሥት ዕቅድ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን አቅጣጫዎች በግልጽ እንደሚያስቀምጡም ይጠበቃል፡፡

በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችንም ያብራራሉ፡፡ ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ የፕሬዚዳንቱን ንግግር እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሁሉም አማራጮች ጉባኤውን በቀጥታ ለሕዝብ ያደርሳል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review