ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል።

ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው።

በመሪዎች መነጽር ሲታይ ቃል ቀላል ድምፅ ሳይሆን፤ ታሪክን የሚወስን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይር እና ሀገርን የሚገነባ የኃይል ምንጭ ነው። በመሪዎች ቃል ውስጥ ህዝብ የሀገርን ተስፋና የመሪዎቹን ርዕይ እንዲቃኝ ያስችላል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከ2017 እስከ 2018 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች ዳግም «ከመስከረም እስከ መስከረም» በተሰኘው መጽሐፍ 8ኛ ቅጽ በይፋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

እርስዎም በመጽሐፉ ዘልቀው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ አቅጣጫ ሀገር ለማቅናት የተጓዟቸውን የዓመት ጉዞ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ቁልፍ ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን አቅጣጫ ጠቋሚ መልዕክቶች ይቃኙ።

ሙሉ መጽሐፉን ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:-

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review