ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም

ወጣቶች የራሳቸው ባልሆኑ ጉዳዮች ሳይጠመዱ በሰላም ግንባታ ላይ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወጣቶች ለውይይት እና ለሰላም ግንባታ የሚኖራቸውን አሰተዋጽኦ በተመለከተ ከሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተ-ዕምነቶች ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአሜን ኢትዮጵያ ጋር በጋራ ከወጣቶች ጋር ባካሄዱት መድረክ ወጣቶች በበጎ ተጠቃሚነታቸው ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።

በመድረኩ ወጣቶች ውይይት እና ሰላም ግንባታ ላይ ስለሚኖራቸው ሚና ስልጠና የሰጡት የአሜን ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደጀኔ፤ በወጣቶች በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ላይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮሀንስ ግርማ በበኩላቸው፤ ለሰላም የወጣቶች ሚና የላቀ ስለመሆኑ አንስተው ይህን መሰል መድረኮች ፋይዳቸው የላቀ ነው ብለዋል።

ወጣቶች የራሳቸው ባልሆኑ ጉዳዮች ሳይጠመዱም በሰላም ግንባታ ላይ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አንስተዋል።

በሀይሉ አያሌው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review