AMN- ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም

በኬንያ እየተከናወነ በሚገኘው የአኖኮ ዞን 5 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች።

በአትሌቲክስ በ1500 ሜትር የተወዳደረችው ኤልሳቤት አማረ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች።

በጎዳና የሳይክል ውድድር ላይ የተሳተፈው ለገሰ ሰለሞን አንደኛ በመውጣት ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቷል።
በተመሳሳይ በጎዳና የሳይክል ውድድር ማህደር ደስታ የነሐስ ሜዳልያ ማምጣት መቻሏን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተገኘው መረጃ ያሳያል።