AMN – ነሐሴ 21/ 2018 ዓ.ም
በሮቤል እና ንቃተህሊና መካከል የተካሄደው የ85 ኪ.ግ. የሚክስድ ማርሻል አርት ፍልሚያ ከባድ ትንቅንቅ የተደረገበት ነው።
ሁለት ዙር በዘለቀው ጠንካራ ግጥሚያ ንቃተህሊና በታላቅ ድል አጠናቋል።
ንቃተህሊና የስፖርቱን እድገትና የወደፊት ተስፋ በማሰብ፣ ይህ የውድድር አይነት በሀገራችን ወደ አደባባይ እንዲመጣና እውቅና እንዲያገኝ በፅናትና በድፍረት የታገለ ተፋላሚ ነው።
በመጀመሪያው ETFC 01 ውድድሩ ያጋጠሙትን ክፍተቶች በትህትና በማረም፣ዝቅ ብሎ በመስራት፣ በረጋ መንፈስ፣በትጋትና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ በመስራት የዛሬውን ስኬት ማግኘት ችሏል።
በአዲሱ መንገሻ