ቱሪዝም የሀገርን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው

AMN – ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም

ባህልን፣ ታሪክንና የተፈጥሮ ሀብትን በማነቃቃት ላይ የተመሠረተው የኢትዮጵያ የቱሪዝም ስትራቴጂ የሀገሪቱን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ በመገንባት ላይ ይገኛል።

መንግሥት ምቹ ሁኔታዎችንና መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ከዘርፉ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራም ይገኛል።

የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው።

የለውጡ መንግሥት ሁለገብ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ባደረገው ሪፎርም ለቱሪዝም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የዘርፉን መሠረት የሚጥሉ ትላልቅ ሥራዎችን አከናውኗል።

ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረትና አቅጣጫ እስከ አሁን በተወሰዱ እርምጃዎች፤ አየር ማረፊያዎችን፣ ሆቴሎችንና የመንገድ ትስስሮችን ማዘመን ተችሏል።

ይህም ኢትዮጵያ ተደብቀው የቆዩ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሀብቶቿን ለዓለም እንድታሳይ አስችሏታል።

በዘርፉ የነበረውን የተሳሳተ አመለካከት ከመሠረቱ የለወጠው ይህ ንቅናቄ፣ ሀገሪቱን የቱሪስቶችና የኢንቨስተሮች ቀዳሚ ማዕከል እያደረጋት ይገኛል።

በዚህም መሠረት የባህል፣ የታሪክና የሰው ሠራሽ ቅርስ ሀብቶችን፣ እንዲሁም የተፈጥሮ ጸጋዎችን መንከባከብ፣ ማልማትና ማስተዋወቅ ላይ ሰፊ ሥራ ተሠርቷል።

የቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ በማግኘት ላይ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቱሪስቶችና የኢንቨስተሮች ማዕከል በመሆን ከዕድገቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆን ጀምራለች።

መንግሥት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሰፊው ትኩረት በመስጠት እየሠራ ይገኛል።

በፍሬሕወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review