አዲስ አበባ ለአፍሪካ ህጻናት ብሩህ ተስፋ እየሆነች ነው

AMN – ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም

አዲስ አበባ ሕፃናትን በተሻለ እንክብካቤ ለማሳደግ ከአህጉሩ በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡ በዚህም ከተማዋ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ሕፃናት ብሩህ ተስፋ እየሆነች ነው፡፡

በከተማዋ እየተተገበሩ ያሉ ሁለገብ የማህበራዊ ልማት ፕሮግራሞች ለሕፃናት አስተዳደግና ለአእምሮ እድገት ምቹ ሁኔታን በመፍጠራቸው፣ አዲስ አበባ ለአፍሪካ አገራት ትልቅ ትምህርትና ተሞክሮ እየሰጠች ነው፡፡

በተለይም በተቀናጀ መልኩ የሚተገበሩት የ«ቀዳማይ ልጅነት» ፕሮጀክትና የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ስራዎች ለሕፃናት ሁለገብ እድገት ትልቅ መሰረት ጥለዋል።

የቀዳማይ ልጅነት ፕሮጀክት ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ፣ በተጠበቀና ፅዱ አካባቢ እንዲጫወቱ እንዲሁም በአእምሮአዊና አካላዊ ብቃታቸው የጎለበቱ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ የጎላ ድርሻ አለው።

ይህ ስኬታማ የፕሮጀክት ተሞክሮና ውጤታማነት የብዙ የአፍሪካ አገራትን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ በርካታ አገራት ይህንን ተሞክሮ ወደራሳቸው በመውሰድና በመተግበር ላይ ይገኛሉ።

የከተማ አስተዳደሩ ሕፃናትን ማዕከል ያደረጉ የትምህርት፣ የጤና እና የምግብ ዋስትና ፕሮግራሞችን አጠናክሮ በመቀጠሉ፣ አዲስ አበባ ሕፃናትን በተሻለ እንክብካቤ በማሳደግ ለአፍሪካ አርአያ ሆናለች፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review