የሰዎች ሰብዓዊ ክብር የተመለሰባት እና ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት አዲስ አበባ

AMN – ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የመኖሪያ መንደሮች የሰውን ልጅ የመኖር ተስፋና በራስ የመተማመን ስሜት የሚሸረሽሩ ሆኖው ቆይተዋል።

ለኑሮ አስቸጋሪ የነበሩ አካባቢዎች ከጥቂት ዓመታት በፊት የመሐል አዲስ አበባ ገጽታ ነበሩ። ዛሬ ግን ይህ ከደረጃ በታች የነበረው የመኖሪያ መንደር ታሪክ ሆኖ ቀርቷል።

በከተማዋ በስፋት እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበት አልፎ የዜጎችን ሥነ-ልቦናዊ ክብር የመመለስ እና ማኅበራዊ ፍትህን የማረጋገጥ ታላቅ ራዕይ ሕያው ማሳያ ሆኗል።

ከነኚህ አስቸጋሪ የመኖሪያ አካባቢዎች የተነሱ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ዘመናዊነትን የተላበሱና ደረጃቸውን የጠበቁ አዳዲስ መንደሮች መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ ቀድሞ የነበራቸው ጠንካራ ማኅበራዊ መስተጋብርና አብሮነት እንዳይበተንና እንዳይላላ በአንድ አካባቢ እንዲሰፍሩ መደረጉ ልማቱን እጅግ ሰው-ተኮር አድርጎታል።

ከዚህም በተጨማሪ እንደ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ያሉ ወሳኝ ማኅበራዊ መሰረተ ልማቶች በአቅራቢያቸው ተሟልተውላቸዋል።

ቀደም ሲል በፀሐይና በዝናብ በጎዳና ዳር ጉሊት ሲሠሩ የነበሩ እናቶችም ዛሬ ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ በዘመናዊ የንግድ ሼዶችና የገበያ ማዕከላት ውስጥ በመነገድ ቋሚ ገቢ እያመነጩ ይገኛሉ።

የኮሪደር ልማቱ ዋና ዓላማ የከተማን መልክ ማደስ ብቻ ሳይሆን፣ ከሰው ልጅ ደረጃ በታች የነበረውን የአኗኗር ዘይቤ ወደ ደረጃው ወደተጠበቀ ሰብዓዊ ክብር ማሸጋገር መሆኑን በተጨባጭ አሳይቷል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review