AMN – ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በታዩት ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴዎች ልምላሜን እየተላበሰች ትገኛለች። ከተማዋን ጽዱ፣ ውብ እና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ አንጻር ከተከናወኑት ሰፊ ስራዎች መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሚና የላቀ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ የደን ሽፋን የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ከመጀመሩ በዊፍ 2 ነጥብ 8 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ላይ የደን ሽፋኑን ወደ 24 በመቶ ማድረስ መቻሉን መረጃዎች ያመላክታሉ።
የአየር ንብረት ለውጥ እና ስነ-ምህዳር ሚዛን ፈጣን የከተሞች ዕድገት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር የሚያስከትለውን የብክለት ጫና ለመቋቋም የአረንጓዴ ልማት ወሳኝ ነው።

የተተከሉ ችግኞች እያደጉ ሲሄዱ የከተማዋን ስነ-ምህዳር ሚዛን በመጠበቅ ለነዋሪዎች ጤናማ አካባቢን እየፈጠሩ ይገኛሉ። ማህበራዊ መስተጋብር እና የህዝብ መዝናኛዎች አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከዛፍ ተከላ ባለፈ ዘመናዊ እና ውብ የህዝብ መናፈሻዎችን እውን አድርጓል።
እነዚህ ስፍራዎች የቤተሰብ መዝናኛዎች፣ የዕረፍት ሰዓት ማሳለፊያዎች እና የማህበራዊ ትስስር ማዕከላት ሆነዋል። በጋራ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብም በዜጎች መካከል የባለቤትነት ስሜትን እና የጋራ ሃላፊነትን አጠናክሯል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአዲስ አበባ የሰጠው ገጽታ የከተማዋ ሁለገብ ዕድገት ማሳያዎች አንዱ ነው።
በወርቅነህ አቢዮ