AMN-ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሃ-ግብር አርሰናል እና ቼልሲ ያደረጉት ተጠባቂ የለንደን ደርቢ ጨዋታ በአርሰናል 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው እና ድንቅ ፉክክር በታየበት ጨዋታ ሞርጋን ሮጀርስ ቼልሲን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር።
በቅርብ ዓመታት ቼልሲ ላይ በሜዳው ከፍተኛ የበላይነት ያለው አርሰናል ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ባስቆጠሯቸው ግቦች ውጤቱን ቀልብሶ ወሳኝ ድል አሳክቷል።
አርሰናል በኤምሬትስ ቼልሲን ባስተናገደባቸው አምስት የመጨረሻ የሊግ ጨዋታዎች ሁሉንም በድል ተወጥቷል።
ያለፈው ዓመት የሊጉ አሸናፊ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ዘንድሮም አጀማመሩን አሳምሮ ሦስቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።
በዣቢ አሎንሶ የሚመራው ቼልሲ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሽንፈት ቀምሷል።
በሸዋንግዛው ግርማ