የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ የማንሰራራት ቀንን በተለያዩ አደባባዮች በድምቀት አከበረ

AMN- ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብቸኛ ወር የሆነችው የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ሀገራዊ ራዕዮችን በሚያሳዩ ስያሜዎች እየተከበሩ የሚገኙ ሲሆን፤ የዛሬው የጳጉሜን 2 ቀንም “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” ቀን በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ተከብሯል፡፡

ይህንኑ ዕለት በተለዩ አውዶች ለማሰብና ለሕዝብ ለማድረስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በተለያዩ አደባባዮች በደምቀት አክብሯል፡፡

ጳጉሜን 2 “የማንሰራራት ቀን” ተብሎ መከበሩ በተጨባጭ እየታዩ ያሉ ሰፋፊ ሀገራዊ ስኬቶችን አመላካች መሆኑን ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተቋማት ግንባታ እና ሌሎች አጠቃላይ ሪፎርሞችን በማድረግ ጠንካራ መሠረት የጣለችበት፤ አሁን ደግሞ የዘላቂ ልማት ትሩፋቶችን ለቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሷን የማንሰራራት ጉዞዋ በግልጽ እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

በተለይም በታዳሽ ኃይል ልማት፣ በከተሞች ገጽታን የመቀየር ሥራዎች እና በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ውጤት ተኮር ተግባራት የተከናወኑበት ወቅት መሆኑ ለቀኑ መበሰር ዋና ምስክሮች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገራት ልዩ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ የጳጉሜን ቀናት ሲሆኑ፣ እነዚህ ቀናትም የተለያየ ትርጉምና ሀገራዊ ራዕይ ተሰጥቷቻ በመከበር ላይ ይገኛሉ፡፡

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review