ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

AMN – መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።

መሪዎቹ በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለውን ትብብር ለማሳደግ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን በማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረዋል።

ለኮፕ 32 በምናደርገው ዝግጅት ያለንን አጋርነት ጨምሮ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ተወያይተናል ብለዋል።

በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋት በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review