ቻይና ብሪክስን በክፍት ምንጭ ኤአይ ለማገናኘት ሀሳብ አቀረበች

You are currently viewing ቻይና ብሪክስን በክፍት ምንጭ ኤአይ ለማገናኘት ሀሳብ አቀረበች

AMN መስከረም 7/2019

ቻይና ብሪክስን በክፍት ምንጭ(open source) ኤአይ ለማገናኘት ሀሳብ ማቅረቧ ተገለጸ።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ሀገራቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከአባል ሀገራት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል አዲስ እቅድ አቅርበዋል።

በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በጋራ ለማልማት እና ለመጠቀም የክፍት ምንጭ ኤአይ ማህበረሰብ እንዲቋቋም ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ቻይና በዚህ የጋራ የኤአይ ትብብር መድረክ የአንበሳውን ድርሻ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

የታቀደው ማህበረሰብ ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎችን በጋራ ለማልማትና ለመተግበር፣ የእውቀት ሽግግር ለማካሄድ እና የቴክኖሎጂ ልውውጥን ለማሳደግ ያለመ ነው።

ከዚህ የኤአይ ትብብር ባሻገር ቻይና የብሪክስ ዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማጠናከር የክላውድ መድረክ እንዲቋቋም፣ የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እንዲሰጥ፣ በስማርት ፋብሪካዎች ልማት ላይ ትብብር እንዲጎለብት እና ባለሙያዎችን ለማሰልጠን አጋርነት እንዲመሰረት ፍላጎት አላት፡፡

በጉባኤው ላይ የብሪክስ ሙሉ አባላት ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን የክፍት ምንጭ ኤአይ ትብብሩ በተለይ የአባል ሀገራቱን የኤአይ ምርምር፣ የሰው ኃይል አቅም እና የቴክኖሎጂ ትብብር ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በተጨማሪም ቻይና የብሪክስ ሀገራት የኢንዱስትሪና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማጠናከር እንዲሁም የተቀናጀ ገበያ ለመገንባት ጥሪ ማቅረቧን የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review