በአፍሪካ ትልቁን ሞዴል A350-1000 አውሮፕላን የምታንቀሳቅስ ብቸኛዋ ሀገር – ኢትዮጵያ

You are currently viewing በአፍሪካ ትልቁን ሞዴል A350-1000 አውሮፕላን የምታንቀሳቅስ ብቸኛዋ ሀገር – ኢትዮጵያ

AMN – መስከረም 2/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን ሞዴል A350-1000 አውሮፕላን የምታንቀሳቅስ ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን A350-1000 አውሮፕላን በፈረንጆቹ ህዳር 2024 የተረከበ ሲሆን፤ ይህንን ሞዴል ያንቀሳቀሰ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ እያንዳንዳቸው እስከ 395 ተሳፋሪዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው አራት A350-1000 አውሮፕላኖች በስራ ላይ ይገኛሉ።

ይህ አውሮፕላን ለረጅም ርቀት በረራ የተነደፈ ሲሆን፤ ወደ 15 ሺህ 557 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የመብረር አቅም እንዳለውም ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም ከቀድሙት አውሮፕላኖች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነዳጅ ቆጣቢ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ለኢትዮጵያ፣ ይህ ስኬት ሀገሪቱ በአፍሪካ ለረጅም ርቀት የአየር ትራንስፖርት ዋና ማዕከል ያላትን ቦታ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም አህጉሪቱን ከመላው ዓለም መዳረሻዎች ጋር በማገናኘት ላይ እንደሚገኝ አፍሪካ ግሎባል ኒውስ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review