በአዲስ አበባ በቀጣይ የምንሰራው ስራ በእያንዳንዱ ዜጋ ህይወት መለወጥ ተጨባጭ ውጤት የሚያመጡ ተግባራት ላይ ትኩረት ይደረጋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በአዲስ አበባ በቀጣይ የምንሰራው ስራ በእያንዳንዱ ዜጋ ህይወት መለወጥ ተጨባጭ ውጤት የሚያመጡ ተግባራት ላይ ትኩረት ይደረጋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN መስከረም 20/2019

በከተማው ምክር ቤት በድጋሜ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ቃለ መሃላ ከፈፅሙ በኃላ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ንግግር አድርገዋል።

በዚህም ዕለቱ የህዝብና የመንግስት አደራን እንደገና የምንቀበልበት ነው ብለዋል ከንቲባዋ።

አዲሱ የከተማው የመንግስት ምስረታና የምክር ቤቱ መክፈቻ ለአዲስ አበባ የላቀ አገልግሎት አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት ጭምር ነው። የመረጣችሁን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዲሁም በተለያየ መንገድ ድጋፋችሁን የገለፃችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጲያዊያን የዴሞክራሲ ስርዓት ልምምዳቸውን ያጎለበቱበት ሂደት መንግስት ለመመስረት አድርሶን ከውነናል። በከተማችን አሁንም ያልተፈቱ ጉዳዮች ቢኖሩም በተሰሩ ስራዎች ተደስቶ ተስፋ የተሰነቀበት እና የብልፅግና ፓርቲ አርቆ አሳቢነት የታየበትም መሆኑንም ገልፀዋል።

በ7ኛው ዙር ምርጫ ያሳካነው በአዲሱ ምክር ቤት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጭምር የመቀመጫ ወንበር ያገኙበት ነው። የከተማዋን ነዋሪዎች በእኩልነት በፍትሃዊነትና በታማኝነት እናገለግላለን ሲሉም ገልፀዋል።

ባለፉት አምስት አመታት አዲስ አበባን እንደስሟ የማድረግ የተገባውን ቃል በተግባር ፈፅመን ከታሰበው በላይ ተሳክቷል። በቀጣይ ደግሞ በነዋሪዎች ህይወት ላይ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን በትኩረት የሚሰራበት እንደሚሆን ከንቲባዋ ተናግረዋልኸ።

የከተማው የቀጣይ ትኩረትም በእያንዳንዱ ዜጋ ህይወት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ዜጋን በክብር የሚያገለግል ተቋም መገንባት፣ዕድልና ሃብት የሚፈጥር ኢኮኖሚን ማስፋትና መፍጠር፣ለኑሮ የምትመች የነዋሪዎቿን ክብር የምትጠብቅ ከተማ እንድትሆን ማስቻል ነው።

ያጠፋነውን እናርማሙን ያጎደልነውን እንሞላለን። የትናንቱን ስኬት እናስቀጥላለን። ሁሉም ሰው ቆሞ ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊ እንዲሆን እናደርጋለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች። – የከንቲባ ጽ/ቤት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review