ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም

ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ለ19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን በማለት እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን ብለዋል፡፡

የ2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነውም ብለዋል፡፡

ከንቲባዋ አክለውም፤ ልዩነቶቻችንን በውይይት እንፍታ፤ አንድነታችንን በመግባባት እናጠናክር፤ ሀገራችንንም በጋራ ጥረት እንገንባ ነው ያሉት፡፡

ዛሬ ሰንደቃችንን ከፍ ስናደርግ፣ ነገ የኢትዮጵያን ክብር፣ ሰላምና ብልጽግና ከፍ ለማድረግ ቃል እንግባ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዜጎቿ አንድነት ትጠናከራለች፤ በጋራ ቁርጠኝነታችንም ለትውልድ ትጸናለች ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review