የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

AMN ጥቅምት 3/2019

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

አልጋ ወራሹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬትን፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይነት ያለው እድገት እና ብልጽግናንም ተመኝተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review