AMN – ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም

በዘንድሮው በጀት ዓመት ከ3 ሚሊዮን በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት አባል ለማድረግ እቅድ መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ የዘንድሮውን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባ አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ ከጥቅምት 1/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 30/2019 ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ነባርና አዲስ አባላት ምዝገባ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ ነባር አባላት እድሳት እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በ2018 በጀት አመት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ከ 3.2 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ ገልጸዋል፡፡
በቅድስት ዳንኤል