AMN – ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 447 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 139 ወንዶች፣ 261 ሴቶች እና 47 ህፃናት ሲሆኑ፣ ከተመላሾች መካከል 47ቱ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡
መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስከ አሁን ከ109 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ የተቻለ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።