AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም
ቼልሲ በ9ኛ ሳምንት የሊግ መርሃግብሩ ማንችስተር ዩናይትድን በስታምፎርድ ብሪጅ አስተናግዶ 2ለ0 አሸንፏል።
ሞርጋን ሮጀርስ በጨዋታ ፣ ኮል ፓልመር በፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠሯቸው ግቦች ቼልሲን አሸናፊ አድርገዋል።
በጨዋታው በዩናይትድ በኩል ተከላካዩ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ 63ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። አርጀንቲናዊው ተከላካይ ሁለተኛ ቢጫ ያየበት ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት የተሰጠበት በመሆኑ ቡድኑን ዋጋ አስከፍሏል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ16 ነጥብ ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ፤ በውድድር ዓመቱ በሊጉ ለአራተኛ ጊዜ የተሸነፈው ዩናይትድ በሰባት ነጥብ 16ኛ ደረጃ ተቀምጧል።