AMN-መስከረም 3/2019 ዓ.ም
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልቅና አምባው የአልቲሜት ቻምፒየን ሺፕ የ5000 ሜትር አሸናፊ ሆናለች።
አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 14:30.36 የሆነ ሰዓት ፈጅቶባታል። ፋንታዬ በላይነህ ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና አለሽኝ ባወቅ በቅደም ተከትል ከ2-5 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
አትሌት ልቅና ወርልድ አትሌቲክስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው የአልቲሜት ቻምፒየን ሺፕ ላይ ድል ያደረገች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።
የውድድሩ አሸናፊ በመሆኗም 150 ሺየአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።
በሸዋንግዛው ግርማ