የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል አቅማቸውን በማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል አቅማቸውን በማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

AMN- ኅዳር 5/2019 ዓ.ም

የምክር ቤት አባላት ከህዝብ የተሰጣቸውን አደራና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል አቅማቸውን በማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ ዙር የህዝብ ተመራጮች ትስስር አደረጃጀት ምስረታና የአሰራር መመሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር፣ ለምክር ቤቱ በህግ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ከመወጣት አንፃር አቅማችንን ማዳበር አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የህዝቡን አደራ በታማኝነት በመወጣት የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የምክር ቤት አባላቱ መዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው ዋና አፈጉባኤዋ አስገንዝበዋል።

ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በአግባቡ ለመወጣት በየደረጃው ያሉ የምክር ቤት አባላትን አቅም ማጠናከርና ማብቃት ሙሉ የሆነ ቁመና እንዲኖራቸው የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ነው ብለዋል።

የምክር ቤቱ አባላት እኩል ከህዝቡ ጋር ችግሩን አንስተው ማውራት ብቻ ሳይሆን፣ ችግር ፈቺ ህግ እንዲያወጡና የወጣውን ህግ ተግባራዊነቱን በመከታተል ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ለኤ ኤም ኤን በሰጡት አስተያየት፣ ለመረጠን ህዝብ፣ ለህገ-መንግስቱ እና ለህሊናችን ተገዥ በመሆን የተሰጠንን አደራ በታማኝነት እንወጣዋለን ብለዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review