AMN- ኅዳር 18/2019 ዓ.ም
ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 3.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጪ ንግድን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያም፣ ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 3.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል።
የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ እድገት ማሳየቱንም አመልክተዋል።

በሶስት ወራት ውስጥ የተገኘው ገቢም ከሀገራዊ ማሻሻያው በፊት ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የአንድ ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ ጋር የሚስተካከል መሆኑን አመልክተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እያላት በአሰራር ውስንነት ተይዛ እንደቆየች የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
በታምራት ቢሻው