ቡና የኢኮኖሚያችን ዋልታ ነው:-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ቡና የኢኮኖሚያችን ዋልታ ነው:-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም

ቡና የኢኮኖሚያችን ዋልታ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በቡና ልማት ያሳየነው የእድገት ርምጃም ይህንኑ ያንፀባረቀ ነው ብለዋል፡፡

እጅግ አስደናቂ የሆነውን አንድ ሚሊዮን ቶን ቡና የማምረት ግባችንን መትተናል።

የሀገር ውስጥ የቡና ተጠቃሚነትም ትርጉም ባለው መልክ እድገት አሳይቷል።

ከተግዳሮቶቻችን ባሻገር በቡና ልማት ዘርፍ የበለጠ ስኬታማ መሆናችንን ቀጥለናል።

በዘርፉ የተሰማሩ ሁሉ ይህን ቁልፍ ኢንደስትሪ የበለጠ ለማሳደግ የየድርሻቸውን እንዲወጡ እጠይቃለሁ።

ባለፉት ስድስት አመታት ለእድገቱ ያለንን ቁርጠኝነት በሚያሳይ ሁኔታ 8.5 ቢሊዮን የቡና ችግኞችን ተክለናል።

ለቡና የእሴት ሰንሰለት የተሳለጠ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ወሳኝ ሲሆን እሴት የመጨመር ተግባርም ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫችን ነው።

በቀጣይም በጠንካራ ስራ እና ፈጠራ ፀንተን ስኬቶቻችንን ማስቀጠል እና ማስፋት ይኖርብናል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review