AMN – ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም
በኦሮሚያ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ከትላንት ጀምረው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት እያደራጁ ይገኛሉ።
ባለድርሻ አካላቱ ያደራጁትን አጀንዳ ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ 25 ተወካዮችን መርጠው በአደራ ያስረክባሉ።
እነዚህ የሚመረጡ 25 ወኪሎች በነገው ዕለት የክልሉን አጀንዳ በዋና መድረክ አቅርበው በማፀደቅ ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል ተብሏል።
በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ከ1ሺ 700 በላይ ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በባለድርሻ አካላቱ ምክክር እየተሳተፉ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የህብረተሰብ ወኪሎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም የልዩ ልዩ ተቋማትና ማህበራት ወኪሎች ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ነገ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡