AMN ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም
ታዋቂው የቪዲዮ ብሎገር ሀሪ ጃጋርድ “7 Continents, 7 Countries, No Excuses” የተሰኘው አስደናቂ ዓለም አቀፍ ጉዞ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን በብቸኝነት ለመጎብኘት መርጧል።
ሀሪ ጃጋርድ በፌስቡክ ከ5 ሚሊዮን በላይ፣ በዩቲዩብ ደግሞ 2.7 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሲሆን በዓለም ዙሪያ በሚያደርጋቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ ጉዞዎቹ ይታወቃል።
ለእ.አ.አ 2026 የጉዞ መርሃ-ግብሩ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት መምረጡ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ እውቅና ሰጥቷል፡፡
ሀሪ “7 Continents, 7 Countries, No Excuses” ጉዞው ኢትዮጵያ ለማንኛውም ዓለም አቀፍ ተጓዥ ቀዳሚ መዳረሻ እንደሆነች አሳይቷል።

ለምርጫው መነሻ ያደረጋቸውን ኢትዮጵያ ያላትን ጥንታዊ ታሪክ፣ አስደናቂ የተፈጥሮ ውበት እና ልዩ እንግዳ ተቀባይነት ነው፡፡
ሀሪ ጃጋርድ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል፣ ጥንታዊ ቅርሶችንና አዲሲቷን አዲስ አበባ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተመልካቾቹ እያጋራ ይገኛል።
ይህ ጉዞ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የቱሪዝም ተመራጭነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በድጋሚ ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤትና የመስተንግዶ ጥግ መሆኗን ለዓለም ለማሳየት በታዋቂ ግለሰቦች የሚደረጉ መሰል ጉዞዎች ለኢኮኖሚው መነቃቃት እና ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑ ይታመናል።