በዓለም አቀፉ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ኮከብ አትሌቶች እና የአትሌቲክስ አመራሮች ልዩ የእራት ፕሮግራም ተካሄደ

You are currently viewing በዓለም አቀፉ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ኮከብ አትሌቶች እና የአትሌቲክስ አመራሮች ልዩ የእራት ፕሮግራም ተካሄደ

AMN – ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ኮከብ አትሌቶች እና የአትሌቲክስ አመራሮች፤ በውቧ አራዳ ፓርክ በነፋሻማ አየር የታጀበ ልዩ የእራት ፕሮግራም በማዘጋጀት የአዲስ አበባ ቆይታቸውን ይበልጥ አስደሳች እና ልዩ አድርገንላቸዋል ሲሉ ተናገሩ።

በአዲስ አበባ በተከሄደው በዓለም አቀፉ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ኮከብ አትሌቶች እና የአትሌቲክስ አመራሮች ልዩ የእራት ፕሮግራም በአራዳ ፓርክ ተዘጋጅቷል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ማማምሻውን በመዲናችን አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቅ ድምቀት በተከናወነው ዓለም አቀፉ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ ለተሳተፉ ኮከብ አትሌቶች እና የአትሌቲክስ አመራሮች፤ በውቧ አራዳ ፓርክ በነፋሻማ አየር የታጀበ ልዩ የእራት ፕሮግራም በማዘጋጀት የአዲስ አበባ ቆይታቸውን ይበልጥ አስደሳች እና ልዩ አድርገንላቸዋል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review