የሳይንስና ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ተማሪዎች እና መምህራን ያላቸውን የፈጠራ አቅም ያሳዩበት ነው – የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

You are currently viewing የሳይንስና ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ተማሪዎች እና መምህራን ያላቸውን የፈጠራ አቅም ያሳዩበት ነው – የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

AMN – ሚያዝያ 17/2018 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ እንደገለጸው፣ ለሁለት ቀናት በአራዳ ፓርክ ሲካሄድ የቆየው 11ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ ተጠናቋል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበዓሉ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት፣ መድረኩ ተማሪዎችና መምህራን ያላቸውን የፈጠራ አቅም ለህዝብ እንዲያሳዩ ምቹ እድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ባሸገር መድረኩ ተማሪዎችና መምህራን እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበትና አዳዲስ ሀሳቦችን የሚያመነጩበት ትልቅ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበራ በበኩላቸው፣ አውደ ርዕዩ በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን የንድፈ ሀሳብ እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር ወሳኝ ድልድይ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም በአውደ ርዕዩ ወደ 3,700 የሚጠጉ የፈጠራ ስራዎች ለዕይታ መቅረባቸውን ተናግረዋል።

“በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው ይህ መርሃ ግብር፣ በውድድሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና መምህራን እውቅና እና ሽልማት በመስጠት ተጠናቋል።

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review