የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደርና ግዙፍ የልማት ሥራዎች ገጽታዋን በመቀየር ረገድ አስደናቂ ለውጥ አሳይተዋል

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደርና ግዙፍ የልማት ሥራዎች ገጽታዋን በመቀየር ረገድ አስደናቂ ለውጥ አሳይተዋል

AMN ሚያዝያ 24/2018

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደርና ግዙፍ የልማት ሥራዎች ገጽታዋን በመቀየር ረገድ አስደናቂ ለውጥ ማሳየታቸውን የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ፡፡

አምባሳደሮቹ እንዳሉት ባለፉት አጭር ጊዜያት ውስጥ በዋና ከተማዋ የታየው ከፍተኛ ለውጥ አስደናቂ ነው።

አዲስ አበባ የገጽታ በመቀየር ለነዋሪዎቿም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ፣ ዘመናዊ እና ውብ ከተማ ለመሆን መቻሏን ተናግረዋል።

ይህ ለውጥ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም መስፋፋቱ ለሀገሪቱ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሮማኒያ አምባሳደር ጁሊያ ፓቲካ፣ በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ተሰርቶ የታየው ለውጥ ለማመን የሚከብድ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደሯ እንደገለጹት፣ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ከተማዋ አስደናቂ ለውጥ ማሳየቷን ተናግረዋል።

በኮሪደር ልማት በተሰራው ስራ ሰፋፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ለእግር ጉዞ የሚሆኑ ውብ ስፍራዎችና ፓርኮች ያሏት ዘመናዊ ከተማ ሆናለች ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢቭስ እስቲቪሊ ካስትሮ በበኩላቸው፤ የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ የላቀ ውበት ከመስጠቱም በላይ ለህዝቡ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በተለይ ለውጭ ሀገር ዜጎች በከተማዋ ውስጥ ለመዘዋወር፣ ለመንዳት እና ለመዝናናት አሁን ያለው ሁኔታ በጣም ቀላል እና ማራኪ መሆኑን መስክረዋል።

በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በቆይታቸው ወቅት የተመለከቱት የኮሪደር፣ የፓርኮች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች አስገራሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተሰሩት ስራዎች እጅግ አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸው፣ ከተማዋ ለመኖርም ሆነ ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን እያደረጋት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ኤር ቫይስ ማርሻል ሲትዋት ናዪማ ደግሞ ለውጡ የታየበትን ፍጥነት አስደናቂ ነው ብለዋል።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ የነበረው ሁኔታ እና አሁን ያለው ለውጥ ሰማይና ምድር መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ ከተማዋን ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ እየሰሩት ያለው ስራ እጅግ የሚደነቅ ነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review