የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግ ገቡ

You are currently viewing የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግ ገቡ

AMN ግንቦት 5/2018

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናዉ አቻቸዉ ከሺ ጂንፒንግ ጋር ለሚያደርጉት ከፍተኛ ውይይት ቤጂንግ ገብተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግ ሲደርሱ በቻይናው ምክትል ፕሬዝዳንት ሀን ዠንግ አቀባበል የተደረገላቸዉ ሲሆን: በቆይታቸውም፣ ከቻይና ጋር በታሪፍ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በኢራን ጦርነት እና አሜሪካ ከታይዋን ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል።

ትራምፕ ወደ ቻይና ያቀኑት በመካከለኛው ምስራቅ እያካሄዱት ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ከፍተኛ ትችት እየቀረበባቸው ባለበት ወቅት ነው።

ጉብኝቱ በመጋቢት ወር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት ምክንያት ሲራዘም መቆየቱ ይታወሳል።

የአሜሪካና ኢራን ጦርነት አሁንም የዓለምን ኢኮኖሚ በእጅጉ እያናወጠዉ ይገኛል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review