7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ: ተአማኒና አካታች ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፌደራል ፖሊስ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ሚናውን እንዲወጣ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አሳሰቡ

AMN – ግንቦት 15/2018 ዓ.ም

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ: ተአማኒና አካታች ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፌደራል ፖሊስ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ሚናውን እንዲወጣ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርሐ ግብሮች ያስተማራቸውን ዕጩ መኮንኖች አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፥ የፌደራል ፖሊስ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚነሱ የፀረ ሠላም ኃይሎችን ድርጊት የማክሸፍ አቅም ገንብቷል ብለዋል።

ዘመናዊ ትጥቆችን በመታጠቅ የፌደራል ፖሊስ ስኬታማ ተቋም መሆኑንም ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በክኅሎት ያደገ ብቁ ሙያተኛ በማፍራት የድርሻውን እየተወጣ ስለመሆኑም ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል።

ለጎረቤት ሀገራት ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቱም በፀጥታ እና ሠላም ዙሪያ በጋራ ለመስራት እንዲሁም የሽብር ድርጊቶችን ለመከላከል ያግዛልም ብለዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ ሳምንት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደሚካሄድ በመግለፅ፤ ምርጫው ሰላማዊ: ተአማኒና አካታች ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፌደራል ፖሊስ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review