የአፍሪካ እና 3ኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነቸውን አዲስ አበባን የሚያገለግለዉ የፖሊስ ሰራዊት ከዘመኑ ጋር የዘመነ እንዲሆን ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

የአፍሪካ እና 3ኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነቸውን አዲስ አበባን የሚያገለግለዉ የፖሊስ ሰራዊት ከዘመኑ ጋር የዘመነ እንዲሆን ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ በየደረጃው የሚገኙ የከተማችን የፖሊስ አመራሮች እና አባላት ያካሄዱት በ100 ቀናት እቅድ የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ማጠቃለያ ግምገማ ላይ ተገኝቼ በርቱ ብያለሁ ብለዋል፡፡

በሪፎርም በተያዙት በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ባለፉት 100 ቀናት እቅድ ትግበራዎች፣ እያደገችና እየዘመነች ከመጣችው የአፍሪካ እና 3ኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነቸው መዲናችን አዲሰ አበባን የሚያገለግል የፖሊስ ሰራዊት ገለልተኛ ሆኖ በህግ እና በህዝብ የተጣለበትን አደራ በአግባቡ የሚወጣ ተቋም ሆኖ እንዲጠናከር፤ በሥነምግባር ክብሩ የተጠበቀ፣ በሰው ሃይል አቋም ብቁ የሆነና በአሰራርም ከዘመኑ ጋር የዘመነ እየሆነ እንዲሄድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩና ነዋሪው ህዝብ አንዳንዶች የሚፈጽሙትን የተቋሙንና የሰራዊቱን ስም የሚያጠለሹ ስህተቶችን እያረማችሁ፤ ጥሩ የሚሰሩትን እያበረታታችሁ ለምትሰሩት መልካም ስራዎች በርቱ እያለ ይደግፋችኋል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review